Teddy_G - ጋሞ ጎፋ ናታ ሞ - መሪር ሃዘን | Gamo - New Ethiopian Music 2024 (Offi...

Teddy_G - ጋሞ ጎፋ ናታ ሞ - መሪር ሃዘን | Gamo - New Ethiopian Music 2024 (Offi...




      ጎፋ ታና ሞ     

ጎፋ ታና ሞ:
ጎፋ ታሳ ታሳ ታና ሞ:
ኦላይ ታና ሞ(2)::

ምነው ምን አገኛት ያቺ የፍቅር አገር:
አረንጕዴው ምድሯ ለምለሙ ዙሪያዋ:
ዛሬ ከፍቶት አዝኖ ገራገሩ ሕዝቧ:
እኔንእኔን... እኔንእኔን... 
እኔን ይክፋኝ ወገኔ::
እኔ ላልቅስልህ እምባ ሞልቶ ባይኔ(2)::

ጎፋ ታና ሞ:
ጎፋ ታሳ ታሳ ታና ሞ:
ኦላይ ታና ሞ(2)::

እናት ሆይ ልጆሽን አተሻል በመጣው መከራ:
ሕዝቡም በጣም አዝኗል ከፍቶታል በጋራ:
ልጅሽ ሄዷል ላይመለስ ሸፍኖታል ጋራ:
ዘልቋል ከእግዜር ቤት ከሰማዩ ዳራ::
በጋሞ ጎፋ ላይ የደረሰው አደጋ መጠነ ሰፊ ነው:
በዚህ ይብቃ በለን አምላክ ሆይ ታረቀን:
ልባችን ተሰብሯል በዝቷል ሃዘናችን:
እምባችንን አብስ አንተው ይቅር በለን:
ጠንክረን እንቁም መፅናናትን ስጠን:: ...
ጎፋ ታና ሞ:
ጎፋ ታሳ ታሳ ታና ሞ:
ኦላይ ታና ሞ(2)::
ሕዝበ ኢትዮጵያ ሆይ በሰሜን በደቡብ በምራብ በምስራቅ ያላችሁ::
አሳዛኝ ቢሆንም የደረሰው አደጋ በደጉ ወገኔ:
ሕይወት ይቀጥላል:
አንድ ሆነን ፍቅርን በመጋራት:
ሆነን እንደ ቤተሰብ ተስፋ በልብ ይዘን:
እንቁም በወኔ:: ...
ጎፋ ታና ሞ:
ጎፋ ታሳ ታሳ ታና ሞ:
ኦላይ ታና ሞ
ጎዳይ ሸንፎ ማሮ:
ጦሳይ አያና እንቴና መንቴቶ:
ሀቅዳጌስታ ሸንፎ ማሮ:
ዳአዋን ዳእርታስ መንተቶ::

     _____ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር_____ 
             ግጥም _ቴዲ ጉልላት 2016

Teddy

To make it clear the most important part of our business

Post a Comment

Previous Post Next Post

Contact Form